የዓለም ዋንጫ በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር አባል አገሮች የወንድ እግር ኳስ ቡድኖች መካከል የሚከናወን ውድድር ነው። ከ፲፱፻፳፪ ዓ/ም ጀምሮ በየአራት ዓመቱ ይካሄዳል። ነገር ግን በሁለተኛው የዓለም ጦርነትምክንያት የ፲፱፻፴፬ ዓ/ም እና የ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ውድድሮች ሲሰረዙ እስካሁን አሥራ ዘጠኝ ውድድሮች ተካሂደዋል። የዋንጫና ደረጃ ጨዋታዎቹ በዓለም በብዙ ተመልካቾች ከሚታዩ የስፖርት ዝግጅቶች አንደኛ ነው። በደቡብ አፍሪቃ የተካሄደው የ ፳፻፪ቱ ፲፱ ኛው የዋንጫ ውድድር በ ፩ ነጥብ ፩ ቢሊዮን ሰዎች እንደታየ ይገመታል።
ውድድሮች[ለማስተካከል]
ዓርማ | ዓመተ ምሕረት | አስተናጋጅ አገር | ተወዳዳሪ ቡድኖች | የዋንጫው ውድድር ቀን | የዋንጫ ቡድኖች | አሸናፊ ቡድን | የጎል ብዛት |
---|---|---|---|---|---|---|---|
![]() | ፲፱፻፳፪ ዓ/ም (1930 እ.ኤ.አ.) | ኡራጓይ | ፲፫ | ሐምሌ ፳፩ ቀን ፲፱፻፳፪ ዓ/ም | ኡራጓይ እና አርጀንቲና | ኡራጓይ | ፬ ለ ፪ |
![]() | ፲፱፻፳፮ ዓ/ም (1934 እ.ኤ.አ.) | ኢጣልያ | ፲፮ | ሰኔ ፩ ቀን ፲፱፻፳፮ ዓ/ም | ኢጣልያ እና ቼኮዝሎቫኪያ | ኢጣልያ | ፪ ለ ፩ |
![]() | ፲፱፻፴ ዓ/ም (1938 እ.ኤ.አ.) | ፈረንሳይ | ፲፭ | ሰኔ ፲ ቀን ፲፱፻፴ ዓ/ም | ኢጣልያ እና ሁንጋሪያ | ኢጣልያ | ፬ ለ ፪ |
![]() | ፲፱፻፵፪ ዓ/ም (1950 እ.ኤ.አ.) | ብራዚል | ፲፫ | ሐምሌ ፯ ቀን ፲፱፻፵፪ ዓ/ም | ኡራጓይ እና ብራዚል | ኡሩጓይ | ፪ ለ ፩ |
![]() | ፲፱፻፵፮ ዓ/ም (1954 እ.ኤ.አ.) | ስዊዘርላንድ | ፲፮ | ሰኔ ፳፭ ቀን ፲፱፻፵፮ ዓ/ም | ጀርመን እና ሁንጋሪያ | ጀርመን | ፫ ለ ፪ |
![]() | ፲፱፻፶ ዓ/ም (1958 እ.ኤ.አ.) | ስዊድን | ፲፮ | ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶ ዓ/ም | ብራዚል እና ስዊድን | ብራዚል | ፭ ለ ፪ |
![]() | ፲፱፻፶፬ ዓ/ም (1962 እ.ኤ.አ.) | ቺሌ | ፲፮ | ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ/ም | ብራዚል እና ቼኮዝሎቫኪያ | ብራዚል | ፫ ለ ፩ |
![]() | ፲፱፻፶፰ ዓ/ም (1966 እ.ኤ.አ.) | እንግሊዝ | ፲፮ | ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓ/ም | እንግሊዝ እና ጀርመን | እንግሊዝ | ፬ ለ ፪ |
![]() | ፲፱፻፷፪ ዓ/ም (1970 እ.ኤ.አ.) | ሜክሲኮ | ፲፮ | ሰኔ ፲፪ ቀን ፲፱፻፷፪ ዓ/ም | ብራዚል እና ኢጣልያ | ብራዚል | ፬ ለ ፩ |
![]() | ፲፱፻፷፮ ዓ/ም (1974 እ.ኤ.አ.) | ጀርመን | ፲፮ | ሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻፷፮ ዓ/ም | ጀርመን እና ሆላንድ | ጀርመን | ፪ ለ ፩ |
![]() | ፲፱፻፸ ዓ/ም (1978 እ.ኤ.አ.) | አርጀንቲና | ፲፮ | ሰኔ ፲፮ ቀን ፲፱፻፸ ዓ/ም | አርጀንቲና እና ሆላንድ | አርጀንቲና | ፫ ለ ፩ |
![]() | ፲፱፻፸፬ ዓ/ም (1982 እ.ኤ.አ.) | እስፓኝ | ፳፬ | ሐምሌ ፪ ቀን ፲፱፻፸፬ ዓ/ም | ኢጣልያ እና ጀርመን | ኢጣልያ | ፫ ለ ፩ |
![]() | ፲፱፻፸፰ ዓ/ም (1986 እ.ኤ.አ.) | ሜክሲኮ | ፳፬ | ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ/ም | አርጀንቲና እና ጀርመን | አርጀንቲና | ፫ ለ ፪ |
![]() | ፲፱፻፹፪ ዓ/ም (1990 እ.ኤ.አ.) | ኢጣልያ | ፳፬ | ሰኔ ፳፱ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ/ም | ጀርመን እና አርጀንቲና | ጀርመን | ፩ ለ ዜሮ |
![]() | ፲፱፻፹፮ ዓ/ም (1994 እ.ኤ.አ.) | አሜሪካ | ፳፬ | ሐምሌ ፰ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ/ም | ብራዚል እና ኢጣልያ | ብራዚል | ፫ ለ ፪ |
![]() | ፲፱፻፺ ዓ/ም (1998 እ.ኤ.አ.) | ፈረንሳይ | ፴፪ | ሐምሌ ፪ ቀን ፲፱፻፺ ዓ/ም | ፈረንሳይ እና ብራዚል | ፈረንሳይ | ፫ ለ ዜሮ |
![]() | ፲፱፻፺፬ ዓ/ም (2002 እ.ኤ.አ.) | ኮርያ እና ጃፓን | ፴፪ | ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ/ም | ብራዚል እና ጀርመን | ብራዚል | ፪ ለ ዜሮ |
![]() | ፲፱፻፺፰ ዓ/ም (2006 እ.ኤ.አ.) | ጀርመን | ፴፪ | ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ/ም | ኢጣልያ እና ፈረንሳይ | ኢጣልያ | ፭ ለ ፫ |
![]() | ፳፻፪ ዓ/ም (2010 እ.ኤ.አ.) | ደቡብ አፍሪቃ | ፴፪ | ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም | እስፓኝ እና ሆላንድ | እስፓኝ | ፩ ለ ዜሮ |
![]() | |||||||
የ፳፻፲ ዓ/ም (2018 እ.ኤ.አ.) የዓለም ዋንጫ በሩሲያ ይካሄዳል። | |||||||
የ፳፻፲፬ ዓ/ም (2022 እ.ኤ.አ.) የዓለም ዋንጫ በኳታር ይካሄዳል። |
Nenhum comentário:
Postar um comentário